am_tn/rom/14/03.md

1.9 KiB

እናንተ የሌላ ሰው አገልጋይ ላይ የምትፈርዱ፣ እናንተ ማን ናችሁ?

ጳውሎስ ይህን ጥያቄ በሌሎች ላይ የሚፈርዱ ሰዎችን ለመገሰጽ ይጠቀምበታል። ይህ በአረፍተ ሃሳብ መልክ ሊጻፍ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ እግዚአብሔር አይደላችሁም፣ እናም የእርሱ አገልጋዮች ላይ ለመፍረድ አልተፈቀደላችሁም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ፣ አንተ

ይህ “አንተ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር የተገለጸ ነው። (የሁለተኛ መደብ ቅርጾች የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ የሚቆመውም የሚወድቀውም በገዛ ራሱ ጌታ ፊት ነው

እዚህ ላይ ጳውሎስ ስለ እግዚአብሔር ሲናገር አገልጋዮች እንዳሉት ጌታ አድርጎ ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “አገልጋዩን ለመቀበልም ሆነ ላለመቀበል መወሰን የሚችለው ጌታው ብቻ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን እንዲቆም ይደረጋል፣ ምክንያቱም ጌታ እርሱ እንዲቆም ያደርገዋልና

ጳውሎስ እዚህ ላይ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው አገልጋይ ከመውደቅ ይልቅ “እንዲቆም ይደረጋል” ሲል ይናገራል። ይህንን በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “ጌታ ግን ይቀበለዋል ምክንያቱም እርሱ አገልጋዮች ተቀባይነት እንዲኖራቸው ማድረግ ይችላል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)