am_tn/rom/13/13.md

2.1 KiB

እናድርግ

ጳውሎስ አንባቢዎቹንና ሌሎች አማኞችን ከራሱ ጋር ያካትታል። (አካታች “እኛ” የሚለውን ተመልከት)

በቀን እንደሚሆን በአግባብ እንመላለስ

ጳውሎስ እንደ እውነተኞች አማኞች መኖርን ለማስረዳት አንድ ሰው በቀን እንደሚመላለስ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ሁሉ ሊያየን እንደሚችል እያወቅን በግልጽነት እንመላለስ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በዝሙት ወይም በማይቆጣጠሩት የፍትወት ምኞት

እነዚህ አሳቦች መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ነው። በትርጉምህ ውስጥ ልታጣምራቸው ትችላለህ። አ.ት፡ “አስጸያፊ የዝሙት ተግባር”

ሁከት

ይህ በሌሎች ላይ ማሴርንና ከሌሎች ሰዎች ጋር መከራከርን ያመለክታል።

ቅናት

ይህ በሌላው ሰው ስኬት ወይም ሌሎች በሚገጥሟቸው ዕድሎች የሚሰማውን አሉታዊ ስሜት ያመለክታል።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት

ጳውሎስ የክርስቶስን የሥነ ምግባር ባህርይ መቀበልን ሰዎች ሊያዩት እንደሚችሉት ውጫዊ ልብሳችን አድርጎ ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ልበሱት

የአንተ ቋንቋ ትዕዛዝን በብዙ ቁጥር የሚገልጽበት አግባብ ካለ እዚህ ጋ ተጠቀምበት።

ለሥጋ አትመቻቹለት

እዚህ ጋ “ሥጋ” የሚያመለክተው እግዚአብሔርን የሚቃወመውን የሰዎችን ራስ - መር ተፈጥሮ ነው። ይህ የሰው ልጆች ኃጢአታዊ ተፈጥሮ ነው። አ.ት፡ “ክፉ ነገሮችን እንዲያደርግ ለአሮጌው ክፉ ልብ አንዳችም ዕድል ከቶ አትስጡት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)