am_tn/rom/13/06.md

1.6 KiB

በዚህ ምክንያት

“መንግሥት ክፉ አድራጊዎችን ስለሚቀጣ”

እናንተ … ለእያንዳንዱ ስጡ

እዚህ ጋ ጳውሎስ የሚናገረው ለአማኞች ነው።

ለባለሥልጣናት

“ለባለሥልጣናት ግብር መክፈል የሚኖርባችሁ ለዚህ ነው”

የሚተጉ

“የሚያስተዳድሩ” ወይም “የሚሠሩ”

ግብር ለሚገባው ግብርን፣ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባው ክብርን።

“ስጡ” የሚለውን ቃል ቀደም ሲል ከነበረው ዐረፍተ ነገር መገንዘብ ይቻላል። አ.ት፡ “ግብር ለሚገባው ግብርን፣ ቀረጥ ለሚገባውም ቀረጥን ስጡ። መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባውም ክብርን ስጡ”

መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባው ክብርን

እዚህ ጋ፣ መፈራትንና ክብርን መስጠት መፈራትና መከበር የሚገባቸውን እነርሱን የመፍራትና የማክበር ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “መፈራት የሚገባቸውን እነርሱን ፍሩ፣ መከበር የሚገባቸውን እነርሱን ደግሞ አክብሩ” ወይም “ልታከብሯቸው የሚገባችሁን አክብሯቸው፣ አክብሮት ልታሳዩአቸው የሚገባችሁንም አክብሮትን አሳዩአቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቀረጥ

ይህ የቀረጥ ዓይነት ነው።