am_tn/rom/13/03.md

2.3 KiB

ስለ

ጳውሎስ የሮሜ 13፡2 ማብራሪያውን ለመጀመርና መንግሥት በአንድ ሰው ላይ ቢፈርድበት ምን እንደሚከተለው ለመንገር ይህንን ቃል ይጠቀማል።

ገዢዎች አስፈሪዎች አይደሉም

መልካም ሰዎችን ገዢዎች እንዲፈሩ አያደርጓቸውም።

ለመልካም ሥራ … ለክፉ ሥራ

ሰዎች በ”መልካም ሥራቸው” ወይም በ”ክፉ” ሥራቸው ተለይተዋል”።

በሥልጣን ላይ ያለን ሰው የማትፈራው መሆን ትፈልጋለህ?

ሰዎች ገዢዎችን ላለመፍራት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲያስቡ ለማድረግ ጳውሎስ ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “ገዢዎችን እንዴት መፍራት እንደማይኖርባችሁ እንድነግራችሁ ፍቀዱልኝ”። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

አድናቆቱን ትቀበላለህ

መንግሥት መልካም የሆነውን ስለሚያደርጉ ሰዎች መልካም ነገር ይናገራል።

እርሱ ያለምክንያት ሰይፍ አይታጠቅም

ይህንን በአዎንታ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “እርሱ ሰይፍ የሚታጠቀው በጣም ጥሩ በሆነ ምክንያት ነው” ወይም “እርሱ ሰዎችን የሚቀጣበት መብት አለው፣ ስለዚህ ሰዎችን ይቀጣቸዋል” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)

ሰይፍ መታጠቅ

ሮማውያን ገዢዎች የሥልጣናቸው ምልክት የሚሆን አጭር ሰይፍ ይታጠቁ ነበር። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የቁጣ ተበቃይ

እዚህ ጋ “ቁጣ” የሚወክለው ሰዎች ክፉ ነገር በሚያደርጉበት ጊዜ የሚቀበሉትን ቅጣት ነው። አ.ት፡ “በክፉ ላይ የመንግሥትን ቁጣ ለመግለጽ ሰዎችን የሚቀጣ ሰው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ስለ ሕሊና ደግሞ እንጂ በቁጣው ምክንያት ብቻ አይደለም

“መንግሥት እንዳይቀጣህ ብለህ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፊት ንጹህ ሕሊና እንዲኖርህ ደግሞ ነው”