am_tn/rom/13/01.md

1.6 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

አማኞች በገዢዎቻቸው ሥር እንዴት መኖር እንዳለባቸው ጳውሎስ ይነግራቸዋል።

ነፍስ ሁሉ ለ . . . ታዛዥ ትሁን

እዚህ ጋ “ነፍስ” ሙሉዉን ሰው በከፊል የሚገልጽ ነው። “ክርስቲያን ሁሉ መታዘዝ አለበት” ወይም “ሁሉም መታዘዝ አለበት”

ከፍተኛ ባለሥልጣናት

“የመንግሥት ኃላፊዎች”

ስለ

ምክንያቱም

ከእግዚአብሔር ካልመጣ በስተቀር ሥልጣን የለም

“ሥልጣን ሁሉ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው”

አሁን ያሉት ባለሥልጣናት በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው

ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በዚያ ያሉት እግዚአብሔር እዚያ ላይ ስላስቀመጣቸው ነው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ያ ሥልጣን

“ያ የመንግሥት ሥልጣን” ወይም “እግዚአብሔር በኃላፊነት ላይ ያስቀመጠው ሰው ሥልጣን”

ይህንን የሚቃወሙ በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ

ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “የመንግሥትን ሥልጣን በሚቃወሙት ላይ እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)