am_tn/rom/12/19.md

2.6 KiB

ለእግዚአብሔር ቁጣ ዕድል ስጠው

ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንዲቀጣቸው ፍቀድለት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ተጽፏልና

ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “አንድ ሰው ጽፎታልና” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በቀል የእኔ ነው፤ እኔ እመልሳለሁ

እነዚህ ሁለቱም ሐረጎች መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ሲሆን እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚበቀል አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “በርግጥ እኔ እበቀላችኋለሁ”

ጠላትህን … አብላው … የሚጠጣውን ስጠው … ይህንን ብታደርግ … ትከምራለህ፣ ክፉን አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ

“አንተ” እና “የአንተ” የሚሉ አገባቦች ሁሉ ለአንድ ሰው እንደሚነገሩ ሆነው ቀርበዋል።

ነገር ግን ጠላትህ ከተራበ … በራሱ ላይ

ጳውሎስ በ12፡20 ላይ ከሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይጠቅሳል። አ.ት፡ “ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ፣ ‘ጠላትህ ከተራበ … በራሱ ላይ …’ ይላል”

አብላው

“ጥቂት ምግብ ስጠው”

በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህ

ጳውሎስ አንድ ሰው በራሳቸው ላይ የእሳት ፍም የሚያፈስባቸው በሚመስልበት ሁኔታ ጠላቶች ስለሚቀበሏቸው በረከቶች ይናገራል። ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፣ 1) “የጎዳችሁ ሰው የማይገባ ነገር እንዳደረገባችሁ እጅግ ተሰምቶት እንዲጸጸት አድርጉት” ወይም 2) “እግዚአብሔር በጠላትህ ላይ የከፋ ፍርድ የሚሰጥበትን ምክንያት እንዲያገኝ አድርገው” የሚሉት ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ

ጳውሎስ “ክፉ”ን እንደ ሰው በመቁጠር ይገልጸዋል። ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉም ትችላለህ። አ.ት፡ “ክፉዎች እንዲያሸንፉህ አትፍቀድላቸው፣ ነገር ግን መልካም የሆነውን በማድረግ ክፉ የሆኑትን አሸንፋቸው” (ሰውኛ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)