am_tn/rom/12/09.md

2.0 KiB

ፍቅር ያለ ግብዝነት ይሁን

ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “ሰዎችን በቅንነትና በእውነተኝነት መውደድ ይኖርባችኋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ፍቅር

እዚህ ጋ ጳውሎስ የሚጠቀምበት ቃል የሚያመለክተው ከእግዚአብሔር በሚመጣውና ራስን በማይጠቅምበት ጊዜም እንኳን ለሌሎች በሚደረግ መልካም ነገር ላይ የሚያተኩረውን የፍቅር ዓይነት ነው።

የወንድማማች ፍቅር ቢሆን አጥብቃችሁ ተዋደዱ

እዚህ ጋ ጳውሎስ አማኞች ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባቸው ለመንገር እያንዳንዳቸው “. . . ሁኑ” የሚል ቅርጽ ያላቸው ዘጠኝ ዓይነቶችን መዘርዘር ይጀምራል። አንዳንዶቹን ዝርዝሮች “. . . አድርጉ” ብለህ መተርጎም ይኖርብህ ይሆናል። ዝርዝሩ እስከ ሮሜ 12፡13 ይቀጥላል።

የወንድማማች ፍቅር ቢሆን

“እንደ እናንተው አማኞች የሆኑትን መውደድን አስመልክቶ”

ፍቅር

ይህ የወንድማማች ፍቅር ወይም የጓደኛ ወይም የቤተሰብ ፍቅር የሚል ትርጉም ያለው ሌላ ቃል ነው። ይህ በጓደኛሞች ወይም በዘመዳሞች መካከል ያለ ተፈጥሮአዊና ሰብአዊ ፍቅር ነው።

አጥብቃችሁ ተዋደዱ

ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “ፍቅርን አሳዩ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

አክብሮትን በሚመለከት እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ

“እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ፣ አክብሮትንም አሳዩ” ወይም “አማኝ ባልንጀሮቻችሁን በማክበር ክብርን ስጧቸው”