am_tn/rom/12/06.md

1.3 KiB

እንደተሰጠን ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን

ጳውሎስ አማኞች ያሏቸው ልዩ ልዩ ችሎታዎች ከእግዚአብሔር በነጻ የተሰጡ ስጦታዎች መሆናቸውን ይናገራል። ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ልዩ ልዩ ነገሮችን ለእርሱ እንድናደርግለት ለእያንዳንዳችን ችሎታዎችን በነጻ ሰጥቶናል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንደተሰጠው የእምነት መጠን ያድርግ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “እግዚአብሔር ከሰጠን የእምነት መጠን ያላለፈ ትንቢትን ይናገር” ወይም 2) “ከእምነታችን አስተምህሮ ጋር የሚስማማ ትንቢት ይናገር” የሚሉት ናቸው።

የአንዱ ስጦታ መስጠት ከሆነ

እዚህ ጋ “መስጠት” የሚያመለክተው ገንዘብንና ሌሎችንም ነገሮች ለሰዎች መስጠትን ነው። ይህንን ፍቺ በትርጉምህ ውስጥ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “አንድ ሰው ገንዘብን ወይም ሌሎች መገልገያዎችን ለተቸገሩ ሰዎች የመስጠት ስጦታ ከተሰጠው”