am_tn/rom/12/03.md

1.4 KiB

ለእኔ በተሰጠኝ ጸጋ ምክንያት

እዚህ ጋ “ጸጋ” የሚያመለክተው ሐዋርያና የቤተ ክርስቲያን መሪ እንዲሆን እግዚአብሔር ጳውሎስን ስለመምረጡ ነው። ይህንን በትርጉምህ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። ደግሞም ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “ምክንያቱም ሐዋርያ እንድሆን እግዚአብሔር በነጻ መርጦኛል”

በመካከላችሁ ያሉ እያንዳንዳቸው ማሰብ ከሚገባቸው በላይ ስለ ራሳቸው እንዳያስቡ

“ከመካከላችሁ ማናቸውም ቢሆኑ ከሌሎች ሰዎች እንደሚሻሉ እንዳያስቡ”

ይልቁንም በጥበብ እንዲያስቡ

“ነገር ግን ስለ ራሳችሁ በምታስቡት ጥበበኞች እንድትሆኑ”

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ በሰጠው የእምነት መጠን

እዚህ ጋ ጳውሎስ የሚያመለክተው፣ በእግዚአብሔር ላይ ካላቸው እምነት ጋር ተያይዞ አማኞች ስለሚኖራቸው የተለያዩ ችሎታዎች ነው። አ.ት፡ “በእርሱ ላይ ባላችሁ እምነት ምክንያት እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ የተለያዩ ችሎታዎችን ስለሰጣችሁ”