am_tn/rom/12/01.md

2.0 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ጳውሎስ የአማኝ ሕይወት ምን መሆን እንዳለበትና እንዴት ማገልገል እንዳለበት ይናገራል።

ወንድሞች ሆይ፣ ስለዚህ በእግዚአብሔር ምህረት እለምናችኋለሁ

እዚህ ጋ፣ “ወንድሞች” የሚያመለክተው ወንዶችንና ሴቶች አማኞችን ነው። አ.ት፡ “አማኞች ሆይ፣ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ታላቅ ምህረት ምክንያት አጥብቄ እለምናችኋለሁ”

ሰውነታችሁን ሕያው መስዋዕት አድርጋችሁ እንድታቀርቡ

ጳውሎስ እዚህ ጋ “ሰውነት” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው ሙሉውን ሰው ለማመልከት ነው። ጳውሎስ በክርስቶስ ሆኖ እግዚአብሔርን በፍጹምነት የሚታዘዘውን አማኝ አይሁዶች አርደው ለእግዚአብሔር ከሚሰዉት እንስሳ ጋር እያነጻጸረ ነው። አ.ት፡ “በቤተ መቅደሱ መሰዊያ ላይ ታርዳችሁ በምትሰዉበት መልኩ ሕያው ሆናችሁ ሳላችሁ ራሳችሁን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር እንድታቀርቡ”

እግዚአብሔር የሚቀበለው፣ ቅዱስ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ለእግዚአብሔር ብቻ የምታቀርቡትና እርሱን ደስ የሚያሰኘው መስዋዕት” ወይም 2) “ንጹህ ሥነ ምግባር ስለሆነ እግዚአብሔር የሚቀበለው” የሚሉት ናቸው።

ይህ ምክንያታዊ አገልግሎታችሁ ነው

“ይህ እግዚአብሔርን የማምለክ ትክክለኛው መንገድ ነው”

ይህንን ዓለም አትምሰሉ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ዓለም እንደሚያደርገው አታድርጉ” ወይም 2) “ዓለም በሚያደርገው መልኩ አታስቡ” የሚሉት ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)