am_tn/rom/11/33.md

1.5 KiB

ኦ! የእግዚአብሔር ጥበብና ዕውቀት ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው!

እዚህ ጋ የ “ጥበብ” እና “ዕውቀት” መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ነው። አ.ት፡ “ከእግዚአብሔር ጥበብና ዕውቀት የሚገኙት ብዙ ጥቅሞች እንዴት የሚያስደንቁ ናቸው!”

ፍርዶቹ እንዴት የማይመረመሩ ናቸው፣ መንገዶቹም ከመታወቅ በላይ ናቸው

“እርሱ የወሰናቸውን ነገሮችና በእኛ ላይ የሚፈጽምባቸውን መንገዶቹን ለመረዳት በፍጹም አንችልም”

የጌታን አሳብ ያወቀ ወይም አማካሪው የሆነ ማነው?

እንደ ጌታ ጥበበኛ የሆነ ማንም እንደሌለ አጽንዖት ለመስጠት ጳውሎስ ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። ይህንን እንደ መግለጫ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “የጌታን አሳብ ያወቀ ማንም የለም፣ አማካሪው የሆነም ማንም የለም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

የጌታን አሳብ

እዚህ ጋ “አሳብ” ነገሮችን ማወቅ ወይም ስለ ነገሮች ማሰብ የሚለውን ገላጭ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ጌታ የሚያውቀውን ሁሉ” ወይም “ጌታ ስለሚያስብለት ጉዳይ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)