am_tn/rom/11/28.md

2.1 KiB

ስለ የምሥራቹ ከሆነ

ጳውሎስ የምሥራቹን የሚጠቅስበትን ምክንያት ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “አይሁዶች የምሥራቹን ቃል ስለ ተቃወሙ”

በእናንተ ምክንያት ጠላቶች ናቸው

የማን ጠላቶች እንደሆኑና ይህም እንዴት በአሕዛብ ምክንያት ሊሆን እንደቻለ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ስለ እናንተ የእግዚአብሔር ጠላቶች ናቸው” ወይም “እናንተ ደግሞ የምሥራቹን እንድትሰሙ እግዚአብሔር እንደ ጠላት ቆጠራቸው”

ስለ ምርጫ ከሆነ

ጳውሎስ ስለ ምርጫ የሚያነሣበትን ምክንያት ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አይሁዶችን መርጦአቸዋልና” ወይም “ምክንያቱም እግዚአብሔር አይሁዶችን ስለ መረጣቸው ነው”

በአባቶቻቸው ምክንያት የተወደዱ ናቸው

አይሁዶችን ማን እንደሚወዳቸውና ጳውሎስ ለምን አባቶቻቸውን እንደሚጠቅስ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። ደግሞም ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ሊያደርግላቸው ተስፋ በመስጠቱ ምክንያት አሁንም ይወዳቸዋል”

የእግዚአብሔር ስጦታና ጥሪው የማይለወጥ ነውና

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሊሰጣቸው ቃል ስለገባላቸው መንፈሳዊና ቁሳዊ በረከቶች ጳውሎስ እንደ ስጦታዎች በመቁጠር ይናገራል። የእግዚአብሔር ጥሪ አይሁዶች የእርሱ ሕዝብ እንዲሆኑ እግዚአብሔር የመጥራቱን ሐቅ ያመለክታል። አ.ት፡ “ሊሰጣቸው ቃል ስለገባላቸው ነገርና የእርሱ ሕዝብ እንዲሆኑ እንዴት እንደጠራቸው እግዚአብሔር በፍጹም አሳቡን አልለወጠም”