am_tn/rom/11/25.md

1.9 KiB

ሳታውቁ እንድትቀሩ አልፈልግም

እዚህ ጋ ጳውሎስ ድርብ አሉታን ይጠቀማል። ይህንን በአዎንታ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “እንድትገነዘቡ በጣም እፈልጋለሁ” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)

ወንድሞች

እዚህ ጋ “ወንድሞች” ማለት ወንዶችንና ሴቶችን ጨምሮ እንደ እርሱ ክርስቲያን የሆኑትን ነው።

እኔ

ተውላጸ ስም የሆነው “እኔ” የሚያመለክተው ጳውሎስን ነው።

አንተ … አንተ … የአንተ

ተውላጸ ስም የሆኑት “አንተ” እና “የአንተ” የሚያመለክቱት አሕዛብ አማኞችን ነው።

በራሳችሁ አሳብ ጥበበኞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ

አሕዛብ አማኞች ካላመኑት አይሁዶች ይልቅ ጥበበኞች እንደሆኑ እንዲያስቡ ጳውሎስ አይፈልግም። አ.ት፡ “ከእነርሱ ይልቅ ጥበበኞች እንደሆናችሁ እንዳታስቡ”

በእስራኤል ከፊል ድንዳኔ ሆነባቸው

ጳውሎስ ስለ “ድንዳኔ” ወይም እልኸኝነት በሰውነት ውስጥ እንዳለ ጠጣር ብልት አድርጎ ይናገራል። አንዳንድ አይሁዶች በኢየሱስ አማካይነት ድነትን ለመቀበል እምቢ ብለዋል። አ.ት፡ “ብዙ እስራኤላውያን እልኸኞች ሆነው ቀጥለዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የአሕዛብ ሙሉነት እስኪመጣ ድረስ

“እስኪመጣ ድረስ” የሚለው ቃል እግዚአብሔር አሕዛብን ወደ ቤተክርስቲያን ማምጣቱን ከጨረሰ በኋላ ጥቂት አይሁዶች እንደሚያምኑ ያመለክታል።