am_tn/rom/11/22.md

2.2 KiB

የእግዚአብሔርን የደግነት ሥራና ጭካኔውን

ምንም እንኳን እግዚአብሔር በታላቅ ደግነት ቢያደርግላቸውም ሊፈርድባቸውና ሊቀጣቸው እንደማያመነታ ጳውሎስ አሕዛብ አማኞችን ያስታውሳቸዋል።

ጭካኔው በወደቁት አይሁድ ላይ መጣ … የእግዚአብሔር ደግነት በአንተ ላይ ይመጣል

የነገር ስም የሆኑትን “ጭካኔ” እና “ደግነት” ለማስቀረት ይህንን እንደገና መጻፍ ይቻላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በወደቁት አይሁድ ላይ ክፉን አድርጎባቸዋል … በአንተ ላይ ግን በደግነት ያደርጋል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

በወደቁት አይሁድ ላይ

የማይገባውን ማድረግ መውደቅ እንደሆነ ተነግሯል። አ.ት፡ “የማይገባውን ያደረጉ አይሁድ” ወይም “በክርስቶስ ለመታመን ፈቃደኛ ያልሆኑት አይሁድ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በደግነቱ ውስጥ ብትቀጥል

የነገር ስም የሆነውን “ደግነት” ለማስቀረት ይህ እንደገና ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “ትክክል የሆነውን ማድረግህን ብትቀጥል እርሱም ለአንተ ደግ መሆኑን ይቀጥላል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ካልሆነ አንተም ደግሞ ትቆረጣለህ

እግዚአብሔር ከፈለገ “ሊቆርጠው” ስለሚችለው ቅርንጫፍ ለመናገር ጳውሎስ እንደገና በዘይቤአዊ አነጋገር ይጠቀማል። እዚህ ጋ “መቆረጥ” አንድን ሰው የመጣል ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “ካልሆነ እግዚአብሔር አንተን ይቆርጥሃል” ወይም “ካልሆነ እግዚአብሔር አንተን ይጥልሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)