am_tn/rom/11/19.md

2.2 KiB

ቅርንጫፎች ተሰብረዋል

እዚህ ጋ፣ “ቅርንጫፎች” የሚያመለክተው ኢየሱስን የተቃወሙትንና አሁን እግዚአብሔር የተዋቸውን አይሁዶችን ነው። ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ቅርንጫፎቹን ሰበራቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

እኔ ገብቼ እንድጣበቅ

ጳውሎስ ይህንን ሐረግ የሚጠቀመው እግዚአብሔር የተቀበላቸውን አሕዛብ አማኞች ለማመልከት ነው። ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “እኔን አስገብቶ ሊያጣብቀኝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የእነርሱ … እነርሱ

ተውላጸ ስም የሆኑት “የእነርሱ” እና “እነርሱ” የሚያመለክቱት ያላመኑትን አይሁዶች ነው።

ነገር ግን በእምነትህ ምክንያት ጸንተህ ቆመሃል

ጳውሎስ የሚናገረው ማንም ሊያንቀሳቅሳቸው እስከማይቻለው ድረስ በታማኝነት ጸንተው ስለቆሙት አሕዛብ አማኞች ነው። አ.ት፡ “ነገር ግን በእምነታችሁ ምክንያት ቆማችኋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር በተፈጥሮአቸው ቅርንጫፍ ለሆኑት ካልራራላቸው ለአንተም አይራራልህም

እዚህ ጋ፣ “በተፈጥሮአቸው ቅርንጫፍ የሆኑት” የሚያመለክተው ኢየሱስን የተቃወሙትን አይሁዶች ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ከሥር ጀምሮ ላደገው፣ የተፈጥሮ ዛፍ ቅርንጫፍ ለሆነው፣ ላላመኑት አይሁድ ካልራራላቸው፣ እንግዲህ ባታምን ለአንተም እንደማይራራልህ ዕወቅ። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)