am_tn/rom/11/17.md

2.3 KiB

አንተ የበረሃ ወይራ ቅርንጫፍ

ተውላጸ ስም የሆነው “አንተ” እና “የበረሃ ወይራ ቅርንጫፍ” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው በኢየሱስ ድነትን የተቀበሉትን አሕዛብ ነው።

ከቅርንጫፎቹ አንዳንዶቹ ቢሰበሩ

እዚህ ጋ፣ ጳውሎስ “የተሰበሩ ቅርንጫፎች” በማለት የሚያመለክተው ኢየሱስን የተቃወሙትን አይሁዶች ነው። ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “አንዱ ጥቂት ቅርንጫፎችን ቢሰብራቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በመካከላቸው ብትጣበቅ

እዚህ ጋ ጳውሎስ “እንደተጣበቁ ቅርንጫፎች” አድርጎ የሚናገረው ስለ አሕዛብ ክርስቲያኖች ነው። ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “በቀሩት ቅርንጫፎች መካከል እግዚአብሔር በዛፉ ላይ አጣብቆሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የበለጸገው የወይራው ዛፍ ሥር

እዚህ ጋ፣ “የበለጸገው ሥር” የእግዚአብሔርን ተስፋ የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በቅርንጫፎቹ አትመካ

እዚህ ጋ፣ “ቅርንጫፎቹ” የእስራኤልን ሕዝብ የሚወክል ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ከጣላቸው የአይሁድ ሕዝብ አንተ እንደምትሻል አትናገር” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሥሩ አንተን ይሸከምሃል እንጂ አንተ ሥሩን አትሸከመውም

ጳውሎስ አሕዛብ አማኞች ቅርንጫፎች መሆናቸውን እንደገና ያመለክታል። እግዚአብሔር ለአይሁድ በገባው የኪዳን ተስፋ ምክንያት ብቻ ያድናቸዋል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)