am_tn/rom/11/01.md

2.0 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

እስራኤል እንደ ሕዝብ እግዚአብሔርን ቢተዉትም ድነት ያለ ሥራ በጸጋ እንደሆነ ይረዱ ዘንድ እግዚአብሔር ይፈልግባቸዋል።

እንግዲህ እላለሁ

“እንግዲህ እኔ ጳውሎስ እላለሁ”

እግዚአብሔር ሕዝቡን ጥሎአቸዋል?

‘የአይሁድ ሕዝብ ልባቸው በመደንደኑ እግዚአብሔር አህዛብን በሕዝቡ ውስጥ አካተታቸው’ በማለት የሚበሳጩ የሌሎች አይሁዶችን ጥያቄ ለመመለስ እንዲያስችለው ጳውሎስ ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እንዲህ አይደለም

“ይህ ሊሆን የማይችል ነው!” ወይም “ያለጥርጥር አልጣላቸውም!” ይህ አገላለጽ ሊሆን እንደማይችል አጥብቆ ይቃወማል። በአንተ ቋንቋ እዚህ ጋ መጠቀም የምትችልበት ተመሳሳይ አገላለጽ ይኖርህ ይሆናል። ይህንን በሮሜ 9፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

የብንያም ጎሳ

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር በ12 ጎሳ ከከፋፈላቸው ከእስራኤል ሕዝብ አንዱ ከሆነው ከብንያም ጎሳ የተገኙትን ነው።

አስቀድሞ ያወቃቸውን

“ከረጅም ጊዜ በፊት ያወቃቸውን”

ኤልያስ እስራኤልን በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እንደከሰሳቸው መጽሐፍ የሚናገረውን አታውቁም?

ይህንን በአድራጊ ድምፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “ኤልያስ እስራኤልን በእግዚአብሔር ፊት በከሰሳቸው ጊዜ ምን ተብሎ በመጽሐፍ እንደ ተጻፈ በእርግጥ ታውቃላችሁ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)