am_tn/rom/10/20.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፥

እዚህ ላይ “እኔ” እና “የእኔ” የሚሉ ቃላት የሚያመለክቱት እግዚአብሔርን ነው።

ከዚያም ኢሳይያስ በድፍረት እንዲህ ብሎ ተናገረ

ይህ ማለት ነብዩ ኢሳይያስ የጻፈው እግዚአብሔር የተናገረውን ነው።

ለማይፈልገኝ ሕዝብ ተገኘሁ

ነቢያት ብዙውን ጊዜ ለወደ ፊት ሊከሰቱ ያሉትን ነገሮች እንደተፈጸመ አድርገው ይናገራሉ። ይህ አጥብቆ የሚያስረዳው ትንቢቱ በእርግጠኝነት እንደሚፈጸም ነው። በሌላ አባባል፥ “የእግዚአብሔር ያልሆኑ ሕዝቦች ምንም እንኳ ባይፈልጉኝ ያገኙኛል”

ተገለጥኩ

“ራሴን አሳወቅኩ”

እርሱ እንዲህ ይላል

“እርሱ” የሚለው የሚያመለክተው በኢሳይያስ በኩል የተናገረውን እግዚአብሔርን ነው።

ቀኑን ሙሉ

ይህ ሐረግ አጥብቆ የሚገልጸው የእግዚአብሔርን ተከታታይ ጥረት ነው። “በተከታታይ”

እጆቼን ለማይታዘዝና ለልበ ደንዳና ሕዝብ ዘረጋው

“እናንተን ለመቀበልና ለመርዳት ሞከርኩ ነገር ግን እርዳታዬን እምቢ ብላችሁ በአለመታዘዝ ሕይወት ቀጠላችሁ።