am_tn/rom/10/18.md

1.7 KiB

ነገር ግን እኔ እላለው፥ “እነርሱ ሰምተው የለም ወይ?” አዎ፤ በእርግጥ ሰምተዋል።

ጳውሎስ በጥያቄ መልክ ያቀረበው ለነገሩ አጽንኦት በመስጠት ነው።ጥያቄውን ወደ ዐረፍተ ነገር መልሳችሁ መተርጎም ትችላላችሁ። በሌላ አባባል፥ “ነገር ግን እኔ እላለሁኝ፥ አይሁዶች በእርግጥ ስለ ክርስቶስ የሚነገረውን መልዕክት ሰምተዋል።

ድምጻቸው በምድር ሁሉ ቃላቸውም በምድር ዳርቻ ሁሉ ተሰራጨ

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ነው፤ ጳውሎስ ሁለቱን የተጠቀመው ነገሩን አጥብቆ ለመንገር ነው። “እነርሱ” የሚለው ሐሳብ የሚያመለክተው ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ እና ኮከቦችን ነው።እዚህ ላይ እነዚህ ስለ እግዚአብሔር ለሕዝቦች እንደሚናገሩ መልዕክተኞች ሰዎች ተደርገው ተገልጸዋል።ይህም የሚያመለክተው የነዚህ መኖር ራሱ ምን ያህል የእግዚአብሔርን ኃይልና ክብር የሚያሳይ እንደሆነ ነው።እዚህ ላይ ጳውሎስ ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሰ መሆኑን ገልጣችሁ ማሳየት ትችላላችሁ። በሌላ አባባል፥ “ቅዱሳት መጻሕፍት ላይ እንደተጻፈው ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ እና ኮከቦች የእግዚአብሔር ኃይልና ክብር ማረጋገጫ ናቸው፤በዓለም ላይ ያሉት ሰዎች ሁሉ እነርሱን አይተው ስለ እግዚአብሔር እውነቱን ያውቃሉ”