am_tn/rom/10/14.md

2.1 KiB

ታዲያ እነርሱ ያላመኑበትን እርሱን እንዴት ሊጠሩት ይችላሉ?

ጳውሎስ ይኸንን ጥያቄ የተጠቀመው የክርስቶስን የምሥራች ቃል ወዳልሰሙት ሰዎች የማድረስን አስፈላጊነት አጥብቆ ለማስገንዘብ ነው። “እነርሱ” የሚለው ቃል ገና የእግዚአብሔር ሕዝብ ያልሆኑትን ያመለክታል።በሌላ አባባል፥ “በእግዚአብሔር የማያምኑት የእርሱን ስም ሊጠሩ አይችሉም”

ስለ እርሱ ባልሰሙት በእርሱ እንዴት ሊያምኑ ይችላሉ?

ጳውሎስ ለተመሳሳይ ምክንያት ሌላ ጥያቄ ይጠቀማል። በሌላ አባባል፥ “የእርሱን መልዕክት ያልሰሙ ከሆነ በእርሱ ሊያምኑ አይችሉም”

ማመን

ይህ ማለት ያ ሰው ያለው እውነት መሆኑን መመስከር ማለት ነው።

የሚሰብክ ሳይኖር እንዴት ሊሰሙ ይችላሉ?

ጳውሎስ ለተመሳሳይ ምክንያት ሌላ ጥያቄ ይጠቀማል።በሌላ አባባል፥ “ሰው ካልነገራቸው የእርሱን መልዕክት ሊሰሙ አይችሉም”

ታዲያ ካልተላኩ እንዴት ልሰብኩ ይችላሉ?

ጳውሎስ ለተመሳሳይ ምክንያት ሌላ ጥያቄ ይጠቀማል። “እነርሱ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔር የሆኑትን ያመለክታል። በሌላ አባባል፥ “የሆነ ሰው ካልላካቸው መልዕክቱን ለሌሎች መንገር አይችሉም”

አስደሳች የሆነውን መልካም ዜና ከቦታ ቦታ ሄደው የሚያበሥሩ እግሮች በጣም ያማሩ ናቸው።

ጳውሎስ “እግር” የሚለውን አባባል የተጠቀመው መልዕክቱ ወዳልደረሳቸው ለማድረስ የሚጓዙትን ሰዎች ለማመልከት ነው። በሌላ አባባል። “መልዕክተኞች መጥተው የምሥራቹን ዜና ሲነግሩን በጣም አስገራሚ ነው”