am_tn/rom/10/11.md

1.9 KiB

ቅዱሳት መጻሕፍት ላይ እንደተጻፈው

ጳውሎስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሕይወትና ድምፅ እንዳለው አድርጎ ይናገራል። እዚህ ላይ ጳውሎስ የተጠቀመውን የቅዱሳት መጻሕፍት ቃል ጸሐፊውን በግልጽ መጥቀስ ትችላላችሁ። በሌላ አነጋገር፥ “ኢሳያስ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደጻፈው”

በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም

ይህ “የማያምን ሁሉ ያፍራል” ከማለት ጋር ተመጣጣኝ ትርጉም አለው። እዚህ ላይ በአሉታዊ መልኩ የተቀመጠው ለነገሩ አጽንኦት ለመስጠት ነው። በሌላ አባባል፥ “እግዚአብሔር በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ያከብራል”

በአይሁድና እና በግሪክ መካከል ልዮነት የለም

የጳውሎስ ሐሳብ እግዚአብሔር ለሁሉም ሕዝቦች እኩል ያስብላቸዋል።ይህንን ሐሳብ በትርጉማችን ገልጠን ማሳየት እንችላለን። በሌላ አባባል፥ “በዚህ መልኩ እግዚአብሔር ለአይሁድም አይሁድ ላልሆኑትም እኩል ያስብላቸዋል”

ስሙን ለሚጠሩት ሁሉ እርሱ ሁሉን ነገር አለው

እዚህ ላይ “ሁሉን ነገር አለው” ተብሎ የተተረጎመው አባባል እግዚአብሔር በብዙ በረከት ይባርካል ለማለት ነው።ይህን ሐሳብ በትርጉማችን ገልጠን ማሳየት እንችላለን። በሌላ አባባል፥ “እርሱ በእርሱ የሚተማመኑትን በብዙ በረከት ይባርካቸዋል”

የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል

እዚህ ላይ “ስም” የሚለው ቃል ኢየሱስን የሚተካ ነው። በሌላ አባባል፥ “ጌታ በእርሱ የሚተማመኑትን ሁሉ ያድናል”