am_tn/rom/10/06.md

2.2 KiB

ነገር ግን ከእምነት የሚመጣው የእግዚአብሔርን ሐሳብ መፈጸም እንዲህ ይላል

እዚህ ላይ “የእግዚአብሔርን ሐሳብ መፈጸም” የሚለው አባባል መናገር እንደሚችል ሰው ተደርጎ የቀረበ ነው።በሌላ አባባል፥ “ነገር ግን ሙሴ እምነት እንዴት አንድን ሰው በእግዚአብሔር ፊት ሐሳቡን የፈጸመ እንደሚያደርገው ሲጽፍ እንዲህ ብሏል።

በልባችሁ እንዲህ አትበሉ

ሙሴ ለሕዝቡ ሲናገር ለአንድ ሰው እንደሚናገር አድርጎ ያቀርበዋል።እዚህ ላይ “ልብ” የአንድን ሰው አእምሮ ወይም ውስጣዊ ስሜት የሚተካ ነው። በሌላ አባባል፥ “ራሳችሁን እንዲህ አትበሉ”

ወደ ሰማይ የሚወጣ ማነው?

ሙሴ የሚናገራቸውን ሰዎች ለማስተማር በጥያቄ መልክ አቀረበ። ያለፈው ትምህርቱ ላይ “አትበሉ” ሲል ለዚህኛው ጥያቄ አሉታዊ መልስ እንደሚያስፈልገው ያሳያል። ይህን ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ማስቀመጥ ይቻላል፥ “ወደ ሰማይ ሊወጣ የቻለ ማንም የለም”

ይህም ማለት ክርስቶስን ለማውረድ

“ክርስቶስ ወደ ምድር እንዲመጣ ለማድረግ”

ወደ ጥልቅም የሚወርድ ማነው?

ሙሴ የሚናገራቸውን ሰዎች ለማስተማር በጥያቄ መልክ አቀረበ።ያለፈው ትምህርቱ ላይ “አትበሉ” ሲል ለዚህኛው ጥያቄ አሉታዊ መልስ እንደሚያስፈልገው ያሳያል። ይህን ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ማስቀመጥ ይቻላል፥ “ወደ ጥልቁ በመውረድ የሞቱ ሰዎች መናፍስት ያሉበት ቦታ ሊገባ የቻለ ማንም የለም”

ከሙታን

ከሞቱት ሰዎች ሁሉ መካከል ማለት ነው።ይህ አባባል በታችኛው ዓለም የሚገኙትን የሞቱ ሰዎች በአንድ ላይ የሚገልጽ ነው።

ሙት

ይህ ቃል ስለ አካላዊ ሞት ይናገራል።