am_tn/rom/08/31.md

1.6 KiB

እንግድህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር እኛን የሚደግፈን ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?

ጳውሎስ ከላይ ለተናገረው ነገር አጽንኦት ለመስጠት ዐረፍተ ነገሩን በጥያቄ መልክ ያስቀምጣል። በሌላ አባባል፣ "ከዚህ ሁሉ መረዳት ያለብን ነገር ይህ ነው፣ እግዚአብሔር እየረዳን ከሆነ ማንም ሊያሸንፈን አይችልም"

የራሱን ልጅ እንኳ ከሞት ያላተረፈው

ገደብ የለሽና ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ ኃጥአተኛ ከሆነው የሰው ባሕርይ ጋር ለማቀራረብ ቅዱስና ገደብ የለሽ መስዋዕት እንዲሆን እግዚአብሔር አብ የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ መስቀል ላከ። እዚህ ላይ "ልጅ" የሚለው ለኢየሱስ ለእግዚአብሔር ልጅ አስፈላጊ ማዕረግ ነው።

ነገር ግን አሳልፎ ሰጠው

"ነገር ግን በጠላቶቹ እጅ ኣሳልፎ ሰጠው"

ታዲያ ከእርሱ ጋር እንዴት ሁሉን ነገር በነፃ አይሰጠንም?

ጳውሎስ ለተናገረው ነገር አጽንኦት ለመስጠት ዐረፍተ ነገሩን በጥያቄ መልክ ያስቀምጣል። በሌላ አባባል፣ "እርሱ በእርግጠኝነት ሁሉን ነገር በነፃ ይሰጠናል"

ሁሉን ነገር በነፃ ይሰጠናል

“በቸርነቱ ሁሉን ነገር ይሰጠናል"