am_tn/rom/08/23.md

2.0 KiB

እኛ የመጀመርያ መንፈሳዊ ፍሬ አፍርተናል

ጳውሎስ የክርስቲያን አማኞችን መንፈስ ቅዱስ መቀበል ተተክሎና ወቅቱን ጠብቆ ከደረሰው የመጀመርያ ፍሬና አትክልት ጋር ያነጻጽራል። መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ለክርስቲያን አማኞች ከሚሰጣቸው ነገሮች የመጀመርያ መሆኑን በአጽንኦት ለመናገር ነው። በሌላ አባባል፣ “እኛ የመጀመርያውን የእግዚአብሔር ስጦታ ያለን ነን፤ እሱም መንፈስ ቅዱስ ነው”

የእግዚአብሔር ልጅነታችንን መሟላት እየተጠባበቅን፤ እሱም የአካላችን መበዥት

እዚህ ላይ "የእግዚአብሔር ልጅነታችን መሟላት" ማለት የእግዚአብሔር ቤተሰብ ሙሉ አባል ስንሆን ማለት ነው። "መበዥት" የሚለው ቃል እግዚአብሔር ሲያድነን ማለት ነው። በሌላ አባባል፣ "የእግዚአብሔር ቤተሰብ ሙሉ አባል መሆናችንን እየተጠባበቅን ይኸውም እሱ ኣካላችንን ከመበስበስና ከሞት ሲያድን"

እኛ በዚህ የታመነ ተስፋ የዳንን ነን

በሌላ አተረጓጎም፣ “በእርሱ ተስፋ ስላደረግን እግዚአብሔር አዳነን”

ነገር ግን ተስፋ የምናደርገውን ነገር እያየን ከሆነ ተስፋ አይደለም ምክንያቱም የሚያየውን ነገር የሚጠብቅ ማን አለ?

ጳውሎስ የሚጽፍላቸውን ሰዎች "ተስፋ" የሚለው ቃል ምን ማለት እንደሆነ እንዲገነዘቡ በጥያቄ መልክ ተናገራቸው። በሌላ አባባል፣ "ነገር ግን በመታመን እየተጠባበቅን ከሆነ የምንፈልገው ነገር ገና አልሆነልንም ማለት ነው። የሚፈልገውን ካገኘማ ማንም በመታመን አይጠብቅም"