am_tn/rom/08/18.md

1.3 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ሰውነታችን በሚበዥበት ጊዜ እንደሚለወጥ ጳውሎስ እኛ አማኞችን እስከ 8፡25 ባለው በዚህ ክፍል ያስታውሰናል።

ለዚህ

እዚህ ላይ 'አስባለሁ' የሚለውን ሐሳብ ለማጽናት ነው። 'ምክንያቱም' ለማለት አይደለም።

ከ. . . ጋር ለማወዳደር የሚገባቸው እንዳልሆኑ አስባለሁ

በሌላ አተረጓጎም፣ “የአሁኑን መከራ ከዚያ ጋር ማወዳደር አልችልም”.

ሊገለጥ ያለው

በሌላ አተረጓጎም፣ "እግዚአብሔር ሊገልጠው ያለው" ወይም "እግዚአብሔር ሊያሳውቅ ያለው"

የፍጥረት በጉጉት መጠባበቅን እየጠበቀ

ጳውሎስ እዚህ ላይ እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ነገሮች ሁሉ በጉጉት የሆነ ነገር የሚጠብቁ አካላት እንደሆኑ ይናገራል።

ለእግዚአብሔር ልጆች መገለጥ

በሌላ አተረጓጎም፣ "እግዚአብሔር ልጆቹን የሚገልጥባቸውን ጊዜ"

የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች

ይህ ማለት በኢየሱስ ያመኑት ሁሉ፤ "የእግዚአብሔር ልጆች" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።