am_tn/rom/08/06.md

883 B

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ጳውሎስ ሥጋዊ ምኞትን አሁን በእኛ ካለው መንፈስ ጋር ማነፃፀሩን ቀጥሏል።

ሥጋዊ አስተሳሰብ. . . መንፈሳዊ አስተሳሰብ

ጳውሎስ እዚህ ላይ ስለ "ሥጋዊ ምኞት" እና ስለ "መንፈስ" ሕይወት እንዳላቸው አካላት አድርጎ ያቀርባቸዋል። በሌላ አባባል፣ "ኃጢአተኞች ሰዎች እንዴት እንደሚያስቡ. . . መንፈስ ቅዱስን የሚያዳምጡ ሰዎች እንዴት እንደሚያስቡ"

ሞት

ይህ ማለት የአንድ ሰው ከእግዚአብሔር መለየት ማለት ነው።

በሥጋዊ ምኞት የሚመሩ

ይህ የሚያመለክተው ክፉ የሆነው ባሕርያቸው የሚነግራቸውን ነገር የሚሠሩትን ሰዎች ነው።