am_tn/rom/08/03.md

2.5 KiB

ምክንያቱም ከሥጋዊ ባሕርያችን ድክመት የተነሣ ሕጉ ማድረግ ያልቻለውን እግዚአብሔር አደረገ

እዚህ ላይ ሕጉ የኃጢአትን ኃይል ሊሰብር እንደማይችል እንደ አንድ አካል ተደርጎ ተገለጸ። በሌላ አባባል፣ "ሕጉ ኃጢአት ከመሥራት ሊያስቆመን የሚችል ጉልበት ስላልነበረው በኛ ውስጥ ያለው የኃጢአት ጉልበትም በጣም ጠንካራ ስለነበረ እግዚአብሔር ግን ኃጢአት ከመሥራት አስቆመን"

በሥጋዊ ባሕርያችን

"በኃጢአተኛው የሰዎች ባሕርይ"

እሱ. . . ኃጢአተኛ ሥጋዊ ባሕርይ በያዘ አካል ተምሣሌት ልጁን ልኮ . . . ስለ ኃጢአት መስዋዕት እንዲሆን. . . እሱ ኃጢአት እንዲወገድ ፍርድ ሰጠ።

የእግዚአብሔር ልጅ የራሱን አካልና ሰዋዊ ሕይወት ስለኃጢአት የዘላለም መስዋዕት አድርጎ በማቅረብ በኃጢአታችን ምክንያት ሊመጣ ያለውን የእግዚአብሔርን ቁጣ ለዘላለም መልሶታል።

ልጅ

ይህ በጣም አስፈላጊ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ማዕረግ ነው፤

ኃጢአተኛ ሥጋዊ ባሕርይ የያዘ አካል ተምሳሌት

"እንደ ማንኛውም ሰው የኃጢአተኛ ሰው መልክ የያዘ"

ስለ ኃጢአት መስዋዕት እንዲሆን

"ስለ እኛ ኃጢአት መስዋዕት ሊሆን እንዲሞት"

በራሱ አካል ኃጢአት እንዲወገድ ፍርድ ሰጠ

"እግዚአብሔር በልጁ አካል የኃጢአትን ኃይል ሰበረ"

ሕጉ ከኛ የሚፈልገውን መመዘኛ እንዲሟላ

በሌላ አተረጓጎም፣ "ሕጉ ከኛ የሚፈልገውን ነገር ማሟላት እንድንችል"

በሥጋዊ ምኞት አካሄድ የማንራመድ እኛ

በመንገዱ መራመድ የሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር አንድ ሰው ሕይወቱን እንዴት እንደሚመራ የሚገልጽ ነው። ሥጋ የሚለው ቃል ደግሞ ኃጢአተኛውን የሰው ባሕርይ የሚተካ ነው። በሌላ አባባል፣ “ኃጢአተኛ የሆነውን ፍላጎታችንን የማንታዘዝ እኛ”

ነገር ግን በመንፈስ የምንመራ

"ነገር ግን ለመንፈስ ቅዱስ የምንታዘዝ"