am_tn/rom/08/01.md

1.7 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ጳውሎስ ኃጢአት እና መልካም ነገርን በተመለከተ በሕይወቱ ስላለው ትግል መልስ ይሰጣል።

ስለዚህ አሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ላመኑት በጥፋተኝነት ወቀሣ ሥር አይሆኑም።

እዚህ ላይ "የጥፋተኝነት ወቀሣ" የሚለው በሕዝብ ላይ የሚመጣውን ቁጣ ያመለክታል። በሌላ አባባል፣ "እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ያላቸውን ጥፋተኛ ናችሁ ብሎ አይቀጣቸውም”

ስለዚህ

"በዚያ ምክንያት" ወይም "እኔ የነገርኳችው እውነት ስለሆነ"

በክርስቶስ ኢየሱስ በሚገኝ የሕይወት መንፈስ ሕግ

ይህ የሚያመለክተው የእግዚአብሔር መንፈስን ነው። "በክርስቶስ ኢየሱስ የሚገኝ የእግዚአብሔር መንፈስ"

ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ አውጥቷችኋል

ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ መውጣት የሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር የኃጢአትና የሞት ሕግ ተገዢ አለመሆንን ያመለክታል። በሌላ አባባል፣ “የኃጢአትና የሞት ሕግ ከአሁን በኋላ እንዳይገዛችሁ አደረገ”

የኃጢአትና የሞት ሕግ

እነዚህን ትርጉሞች ሊያመለክት ይችላል፣ 1) ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚገፋፋ ሕግ፤ ኃጢአታቸው ደግሞ ሞት ያመጣባቸዋል። በሌላ አባባል፣ “ኃጢአትንና ሞትን የሚያመጣ ሕግ" ወይም 2) ሰዎች ኃጢአት ይሠሩና ይሞታሉ የሚል መርህ