am_tn/rom/07/24.md

1.7 KiB

ከዚህ ሟች ከሆነ አካል ማን ያላቅቀኛል?

ጳውሎስ ይህን ጥያቄ የተጠቀመው የተሰማውን ጥልቅ ስሜት ለመግለጽ ነው። በእናንተ ቋንቋ በመጮህ ወይም ጥያቄ በመሰንዘር ጥልቅ ስሜት የሚገለጽበት መንገድ ካለ እዚህ ጋ አስገቡ። በሌላ አባባል፣ "እኔ አካለ ከሚመኘው ምኞት ነፃ የሚያወጣኝን አንድ ሰው እፈልጋለሁ"

ያላቅቀኛል

“ያድነኛል”

ይህ ሟች ሥጋ

ይህ ተለዋጭ ዘይቤ አካላዊ ሞትን የሚሞተውን አካል የሚያመለክት ነው።

ነገር ግን እግዚአብሔር ይመሰገን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ

ይህ በ7፡24 ላይ ላለው ጥያቄ መልስ ነው።

ስለዚህ እኔ ራሴ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔርን ሕግ እገዛለሁ፤ ይሁን እንጂ በሥጋዊ ምኞት ደግሞ ኃጢአት ለሚሠራበት አካሄድ እገዛለሁ።

እዚህ ቁጥር ላይ አእምሮ እና ሥጋዊ ምኞት የገቡት ምን ያህል ለእግዚአብሔር ሕግ ወይም ለኃጢአት ሥራ አካሄድ እንደሚገዙ በንፅፅር ለማሳየት ነው። በአእምሮ ወይም በዕውቀት አንድ ሰው እግዚአብሔርን ማስደሰትና መታዘዝን ሊመርጥ ይችላል፤ ወይ ደግሞ በሥጋዊ ምኞቱ ወይም በአካላዊ ባሕርይው ለኃጢአት ሊገዛ ይችላል። በሌላ አባባል፣ "አእምሮዬ እግዚአብሔርን ማስደሰት ይመርጣል፤ ሥጋዊ ምኞቴ ግን ለኃጢአት መገዛትን ይመርጣል"