am_tn/rom/07/15.md

1.9 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር፣

ጳውሎስ በሥጋዊ ምኞቱ እና በእግዚአብሔር ሕግ መካከል (በክፉ እና በመልካም መካከል) በውስጡ ስለሚካሄድ ፍልሚያ ይናገራል።

እኔ ስላማደርገው ነገር በግልጽ አላውቅም

"እኔ አንዳንድ የማደርጋቸውን ነገሮች ለምን እንደማደርጋቸው እርግጠኛ አይደለውም”

እኔ ለማደርገው

ምክንያቱም እኔ የማደርገው

እኔ ማድረግ የምፈልገውን አላደርግም

“አላደርግም” የሚለው ቃል ተጋንኖ የተነገረው ለነገሩ አጽንኦት ለመስጠት ሲባል ነው። ጳውሎስ ማድረግ የሚፈልገውን የሚደርገው በፈለገው ጊዜ ሁሉ አይደለም ወይም ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ ማድረግ የማይፈገውን ነገር ያደርጋል። በሌላ አባባል፣ "እኔ ማድረግ የሚፈለገውን የማደርገው ሁል ጊዜ አይደለም"

ማድረግ የምጠላውን ነገር አደርጋለሁ

“አደርጋለሁ” የሚለው ቃል በውስጡ የያዘው ሐሳብ ጳውሎስ ሁል ጊዜ ማድረግ የሚጠላውን ነገር ማድረጉን ነው። ይህም ተጋንኖ የተነገረው ለነገሩ አጽንኦት ለመስጠት ሲባል ነው። ጳውሎስ ማድረግ የማይፈልገውን ነገር ደጋግሞ ያደርጋል። በሌላ አባባል፣ "አንዳንድ ጊዜ የማደርጋቸው ነገሮች መልካም አለመሆናቸውን የማውቃቸው ነገሮች ናቸው"

ነገር ግን እንዲህ ባደርግ

"ይሁን እንጂ እንዲህ የማደርግ ከሆነ"

እኔ በሕጉ እስማማለሁ።

"የእግዚአብሔር ሕግ መልካም መሆኑን አውቃለሁ"