am_tn/rom/07/13.md

1.6 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ጳውሎስ በውስጣዊው ሰውነቱ ባለው ኃጢአት እና የእግዚአብሔርን ሕግ በሚያውቀው አእምሮው መካከል (በኃጢአት እና በመልካም ሐሳቡ መካከል) በውስጡ ስለሚካሄደው ፍልሚያ ይናገራል።

እንግዲህ

ጳውሎስ አዲስ ርዕስ እያስተዋወቀ ነው።

መልካም የሆነው ነገር ሞት አመጣብኝ እንዴ?

ጳውሎስ ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ለነገሩ አጽንኦት ለመስጠት ነው።

መልካም የሆነው ነገር

ይህ የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ሕግ ነው።

ሞት አመጣብኝ።

“እንዲሞት አደረገኝ”

ይህ ፈጽሞ አይሁን

ይህ አገላለጽ ለቀደመው ማሳመኛ ጥያቄ በጣም ጠንከር ያለ አሉታዊ መልስ ይሰጣል። በራሳችሁ ቋንቋም በዚህ ቦታ አስገብታችሁ የሚትጠቀሙት ተመሳሳይ አገላለጽ ሊኖራችሁ ይችላል።በሌላ አባባል፣ “ታዲያ ይህማ እውነት አይደለም"

ኃጢአት. . .ሞትን በሕይወቴ አመጣ

ጳውሎስ ኃጢአትን በራሱ የሆነ ነገር ሊያደርግ እንደሚችል አካል አድርጎ ያየዋል።

ሞትን በሕይወቴ አመጣ

"ከእግዚአብሔር ለየኝ"

በእግዚአብሔር ትዕዛዝ አማካይነት

"ምክንያቱም እኔ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ስላልፈጸምኩ"