am_tn/rom/07/11.md

1.5 KiB

ኃጢአት የተሰጠውን ትዕዛዝ እንደ ዕድል በመጠቀም አታለለኝ። በትዕዛዙም ላይ ተመሥርቶ ሞት አመጣብኝ።

በሮሜ 7፡7-8 ላይ እንደተጠቀሰው ጳውሎስ ኃጢአት 3 ነገሮች ማድረግ እንደሚችል ይገልጻል፣ ዕድልን መጠቀም፣ ማታለል እና መግደል። "ኃጢአትን መሥራት ስለፈለኩ በአንድ ጊዜ ኃጢአትንም እየሠራሁ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መታዘዝ እችላለሁ ብዬ እያሰብኩኝ ራሴን አታለልኩ ነገር ግን ለእርሱ ባለመታዘዜ ምክንያት እግዚአብሔር እኔን ከራሱ በመለየት ቀጣኝ"

ኃጢአት

ኃጢአት ለመሥራት ያለኝ ምኞት

ትዕዛዙን እንደ ዕድል በመጠቀም

ጳውሎስ ኃጢአትን የሆነ ነገር ሊያደርግ ከሚችል አካል ጋር ያነፃፅራል። በሮሜ 7፡8 ላይ የሰጣችሁትን ትርጉም ተመልከቱ።

ሞት አመጣብኝ

ጳውሎስ ኃጢአትን የሆነ ነገር ሊያደርግ ከሚችል አካል ጋር ያነፃፅራል። ጳውሎስ በኃጢአተኞች ላይ የሚመጣው የእግዚአብሔር ፍርድ አካላዊ ሞት እንደሚያስከትል አድርጎ ይናገራል። በሌላ አባባል፣ "እኔን ከእግዚአብሔር ለየኝ"

ቅዱስ

በሥነ ምግባር ፍጹም የሆነ፣ ኃጢአት የሌለበት