am_tn/rom/07/07.md

1.4 KiB

እንግዲ ምን እንላለን?

ጳውሎስ አዲስ ርዕስ እያስተዋወቀ ነው።

ይህ ፈጽሞ አይሁን።

“ታዲያ ይህማ እውነት አይደለም" ይህ አገላለጽ ለቀደመው ማሳመኛ ጥያቄ በጣም ጠንከር ያለ አሉታዊ መልስ ይሰጣል። በራሳችሁ ቋንቋም በዚህ ቦታ አስገብታችሁ የሚትጠቀሙት ተመሳሳይ አገላለጽ ሊኖራችሁ ይችላል። በሮሜ 9፡14 ላይ ምን ብላችሁ እንደተረጎማችሁ ተመልከቱ።

ሕግ ባይኖር ኖሮ ኃጢአት ምን እንደሆነ ባላወቅኩ ነበር። በሕግ አማካይነት ለይቼ ባላውቀው ኖሮ. . . ነገር ግን ኃጢአት አጋጣሚውን ተጠቅሞ. . . ሥጋዊ ምኞትን ቀሰቀሰ።

ጳውሎስ ኃጢአትን ሊንቀሳቀስና ሊሠራ ከሚችል ሰው ጋር ያነፃፅራል።

ኃጢአት

"ኃጢአት ለመሥራት ያለኝ ምኞት"

ሥጋዊ ምኞት

ይህ አባባል የሰው የሆነውን ነገር ለመውሰድ መፈለግንና ክፉ የሆነ የወስብ ምኞትን ያጠቃልላል።

ሕግ ከሌለ ኃጢአት የሞተ ነው።

"ሕግ ባይኖር ኖሮ ሕግን መተላለፍ አይኖርም ነበር፤ ይህ ማለት ደግሞ ኃጢአት የሚባል አይኖርም ነበር ማለት ነው።