am_tn/rom/07/04.md

1.7 KiB

ስለዚህ ወንድሞች

ይህ ወደ ሮሜ 7፡1 ለማመልከት ነው።

ወንድሞች

ይህ ማለት ክርስቲያን ወገኖች ማለት ነው፤ወንዶችንም ሴቶችንም ያጠቃልላል።

በክርስቶስ አካል አማካይነት በሞታችው ጊዜ ለሕግም ደግሞ የሞታችው ሆናችኋል

በሌላ አተረጓጎም፣ "በክርስቶስ በኩል በመስቀል ላይ በሞታችው ጊዜ ለሕግም ደግሞ ሞታችኋል"

ከሙታን እንዲነሣ ለተደረገው ለእርሱ

“ከሙታን እንዲነሣ ተደረገ” የሚለው አባባል እንደገና በሕይወት ወደ መኖር መመለስን ያመለክታል። በሌላ አባባል፣ “እግዚአብሔር እንደገና በሕይወት ወደ መኖር ለመለሰው ለእርሱ” ወይም “እግዚአብሔር ከሙታን መካከል ላስነሣው ለእርሱ”

ለእግዚአብሔር ፍሬ ልናፈራ እንችላለን

እዚህ ላይ "ፍሬ" የሚለው ተለዋጭ ዘይቤአዊ አነጋገር እግዚአብሔርን የሚያስደስቱ ተግባራት መፈጸምን ያመለክታል። "እግዚአብሔርን የሚያስደስት ተግባር ልንፈጽም እንችላለን"

ሞትን የሚያስከትል ፍሬ ልናፈራ ሆነ

እዚህ ላይ "ፍሬ" የሚለው ተለዋጭ ዘይቤአዊ አነጋገር “የአንድ ሰው የድርጊቱ ውጤት” ወይም “በአንድ ሰው ድርጊት ምክንያት የመጣ” ማለት ነው። በሌላ አባባል፣ “ውጤቱ መንፈሳዊ ሞት ሆነ” ወይም “መንፈሳዊ ሞትን አመጣብን”