am_tn/rom/07/02.md

1.2 KiB

ያገባች ሴት በሕግ ከባሏ ጋር ተጣምራለች

እዚህ ላይ “በሕግ ከባሏ ጋር ተጣምራለች” የሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር አንዲት ሴት ከባሏ ጋር በጋብቻ ሕግ መሠረት አንድነት መፍጠሯን የሚያመለክት ነው። በሌላ አባባል፣ በሕጉ መሠረት ያጋበች ሴት ከባሏ ጋር አንድነት ፈጥራለች”

ያገባች ሴት

ይህ ማንኛውንም ያገባች ሴት ለማመልከት ነው።

እርሷ አመንዝራ ትባላለች።

በሌላ አባባል፣ "እግዚአብሔር እሷን እንደ አመንዝራ ይወስዳታል" ወይም "ሰዎች እሷን አመዝራ ይሏታል"

እርሷ ከሕጉ ነፃ ናት

እዚህ ላይ ከሕግ ነፃ መሆን ማለት ለሕጉ የግዴታ መታዘዝ አይጠበቅም ማለት ነው። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ያገባች ሴት ሌላ ወንድ ማግባት አትችልም ለሚለው ሕግ የግዴታ መታዘዝ አይጠበቅባትም። በሌላ አባባል፣ “እርሷ የግዴታ ለሕጉ መታዘዝ አይጠበቅባትም”