am_tn/rom/06/22.md

1.6 KiB

ነገር ግን አሁን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችው ለእግዚአብሔር ባሮች ሆናችኋል።

በሌላ አባባል፣ “ነገር ግን አሁን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችው የእግዚአብሔር ባሪያ ሆናችኋል” ወይም “ነገር ግን አሁን እግዚአብሔር ከኃጢአት ነፃ አውጥቶአችሁ የራሱ ባርያ አድርጓችኋል”

ነገር ግን አሁን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችኋል

“ከኃጢአት ነፃ መውጣት” የሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር ኃጢአት መሥራት አለመቻልን የሚያመለክት ነው። በሌላ አባባል፣ “ነገር ግን አሁን እግዚአብሔር ኃጢአት ከመሥራት መቆጠብ እንዲትችሉ አደረጋችሁ”

ለእግዚአብሔር ባሮች ሆናችኋል

ለእግዚአብሔር “ባርያ መሆን” የሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር እግዚአብሔርን ማገልገልና ለእርሱ መታዘዝን የሚያመለክት ነው። በሌላ አባባል፣ “እግዚአብሔር እርሱን ማገልገል እንዲትችሉ አደረጋችሁ”

ፍሬአችው መቀደስ ነው

እዚህ ላይ “ፍሬ” የሚለው ዘይቤ “ውጤት” ወይም “ጥቅም” ለማለት ነው። በሌላ አባባል፣ “ጥቅሙ መቀደሳችው ነው” ወይም “ጥቅሙ እናንተ የተቀደሰ አኗኗር መምራታችሁ ነው”

ውጤቱ የዘላለም ሕይወት ነው

“የዚህ ሁሉ ውጤት እናንተ ለዘላለም ከእግዚአብሔር ጋር ትኖራላችሁ”