am_tn/rom/06/17.md

3.5 KiB

ግን እግዚአብሔር ይመስገን!

"ግን እኔ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ!"

እናንተ የኃጢአት ባሪያ ነበራችሁ

ለኃጢአት ባሪያ መሆን የሚለው ተለዋጭ ዘይቤአዊ አነጋገር አንድ ሰው ኃጢአትን ለመሥራት ያለው ፍላጎት ራሱን መከልከል እስከማይችል ድረስ ጠንካራ ሲሆን ማለት ነው። ኃጢአት ሰውዬውን የሚቆጣጠርበት ሁኔታ ውስጥ መግባት ነው። በሌላ አባባል፣ “እናንተ ለኃጢአት እንደ ባርያ ነበራችሁ” ወይም “እናንተ በኃጢአት ቁጥጥር ሥር ነበራችሁ”

ነገር ግን እናንተ ከልባችሁ ታዛዦች ሆናቿል።

እዚህ ላይ "ልብ" የሚለው ቃል እዚህ ላይ የሚያመለክተው የምንሠራውን ሥራ በቅንነት ወይም በታማኝነት መሥራትን ነው። በሌላ አባባል፣ "ነገር ግን እናንተ በእውነት ታዛዦች ሆናችኋል”

የተሰጣችውን የአኗኗር አስተምሮ

"አኗኗር" የሚለው ቃል የሚያመለክተው እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ ወደ መኖር የሚያመራ የኑሮ አካሄድን ነው። አማኝ ክርስቲያኖች አሮጌውን የኑሮ አካሄድ ቀይረው በክርስትና መሪዎች አስተምሮ መሠረት ከአዲሱ የኑሮ አካሄድ ጋር የሚሄድ ኑሮ ይኖራሉ። በሌላ አባባል፣ "የክርስትና መሪዎች ያስተማሯችውን ትምህርት"

ከኃጢአት ነፃ ወጥታችው ነበር

በሌላ አባባል፣ "ክርስቶስ ከኃጢአት ኃይል ነፃ አውጥቶአችሁ ነበር"

ከኃጢአት ነፃ ወጥታችው ነበር

እዚህ ላይ “ከኃጢአት ነፃ መውጣት” የሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር አንድ ሰው ኃጢአትን ለመሥራት ያለውን ጠንካራ ፍላጎት መግታትና ራሱን መከልከል እስከመቻል መድረስን የሚያመለክት ነው። በሌላ አባባል፣ “ኃጢአትን ለመሥራት ያለችው ጠንካራ ፍላጎት ተወግዶአል” ወይም “በኃጢአት ቁጥጥር ሥር ከመሆን ነፃ ወጥታችኋል”

የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚታገለግሉ ባሮች

የእግዚአብሔርን ሐሳብ የማገልገል ባርነት የሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ሐሳብ ለመፈጸም ያለውን ጠንካራ ፍላጎት የሚያመለክት ነው። የእግዚአብሔርን ሐሳብ ለመፈጸም ያለው ፍላጎት ሰውዬውን የሚቆጣጠርበት ሁኔታ እንደማለት ነው። በሌላ አባባል፣ “የእግዚአብሔርን ሐሳብ ለመፈጸም ላላችው ፍላጎት እንደ ባርያ ሆናችኋል” ወይም “አሁን እናንተ የእግዚአብሔርን ሐሳብ በመፈጸም ፍላጎት ቁጥጥር ሥር ናችሁ”

የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚታገለግሉ ባሮች

በሌላ አባባል፣ “ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚታገለግሉ ባሮች አድርጓችኋል” ወይም“ “አሁን እናንተ የእግዚአብሔርን ሐሳብ በመፈጸም ፍላጎት ቁጥጥር ሥር እንዲትሆኑ ክርስቶስ ለውጦአችኋል”