am_tn/rom/06/06.md

1.9 KiB

አሮጌው ሰውነታችን ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሏል

"አሮጌ ሰውነት" የሚለው ተለዋጭ ዘይቤ ሰው በክርስቶስ ከማመኑ በፊት የነበረውን ባሕርይ ያመለክታል። ጳውሎስ አሮጌውን ኃጢአተኛ ሰውነታችን በክርስቶስ ባመንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር በመስቀል ላይ እንደሚሞት ይናገራል። በሌላ አባባል፣ “ኃጢአተኛው ሰውነታችን ከኢየሱስ ጋር በመስቀል ላይ ሞቷል”

አሮጌው ሰውነት

አሮጌው ሰውነት ማለት በአንድ ወቅት የነበረ አሁን ግን የሌለ ሰውነት ማለት ነው።

ኃጢአተኛው ሰውነት

ኃጢአተኛው ሰውነት የሚለው ተምሳሌታዊ ቃል የሚያመለክተው በጥቅሉ ያለውን ኃጢአተኛ ሰውነት ነው። በሌላ አባባል፣ “ኃጢአተኛው ባሕርያችን”

የሚጠፋ ሊሆን ይችላል

በሌላ አተረጓጎም፣ “ሊሞት የሚችል”

ከእንግዲህ በኋላ ለኃጢአት ባሪያ መሆን የለብንም

በሌላ አተረጓጎም፣ “ኃጢአት ከእንግዲህ ወዲህ ሊገዛን አይገባም” ወይም “ከእንግዲህ ወዲህ ለኃጢአት ልንገዛ አይገባም”

ከእንግዲህ በኋላ ለኃጢአት ባሪያ መሆን የለብንም

ለኃጢአት ባሪያ መሆን የሚለው ተለዋጭ ዘይቤአዊ አነጋገር አንድ ሰው ኃጢአትን ለመሥራት ያለው ፍላጎት ራሱን መከልከል እስከማይችል ድረስ ጠንካራ ሲሆን ማለት ነው። ኃጢአት ሰውየውን የሚቆጣጠርበት ሁኔታ ውስጥ መግባት ነው። በሌላ አባባል፣ “ከእንግዲህ በኋላ በኃጢአት ቁጥጥር ሥር ልንሆን አይገባም”