am_tn/rom/04/18.md

977 B

በተስፋ ያለተስፋ አመነ

ይህ ዘይቤያዊ አነጋገር አብርሃም እግዚአብሔርን ያመነው ወንድ ልጅ እንደሚኖረው ተስፋ በማያደርግበት ጊዜ ነው፡፡ “ምንም እንኳን ለእርሱ ልጆች እንደሚኖሩት የማይቻል ቢመስልም እግዚአብሔርን አመነ”

በተነገረው መሠረት

ይህ በአድራጊ ቅርፅ ሊተረጎም ይችላል። “እግዚአብሔር ለአብርሃም እንደ ተናገረው”

ዘሮችህ እንዲሁ ይሆናሉ

እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ሙሉ ተስፋ ግልፅ ሊሆን ይችላል፡፡ “ልትቆጥራቸው ከምትችላቸው በላይ ብዙ ዘሮች ይኖሩሃል”

በእምነት አልደከመም

ይህንን በአዎንታዊ መልኩ ልትተረጉመው ትችላለህ። “ምንም ቢሆን በእምነቱ ጠንካራ ነበር”