am_tn/rom/04/16.md

2.3 KiB

ለዚህ ምክንያት

“ስለዚህ”

ይህ በእምነት ነው

“ይህ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር ቃል የገባውን መቀበል ነው፡፡ “ቃል ኪዳኑን የምንቀበለው በእምነት ነው” ወይም “ቃል ኪዳኑን በእምነት እንቀበላለን”

ቃል ኪዳኑ በጸጋ ላይ ያርፍ ዘንድ

“ቃል ኪዳኑ በጸጋ ላይ ያርፋል” የሚለው የሚወክለው እግዚአብሔር ቃል የገባውን የሚሰጠው በጸጋ መሆኑን ነው። “ስለዚህ የገባው ቃል ኪዳን ነጻ ስጦታ ሊሆን ይችላል፣ ወይም “ስለዚህ ቃል ኪዳኑ በጸጋው ይሆናል ማለት ነው”

ለሁሉም የአብርሃም ዝርያዎች ዋስትና ይሆናል

ይህ በአድራጊ ቅርፅ ሊገለጽ ይችላል። “ሁሉም የአብርሃም ዘሮች እግዚአብሔር እንደሚሰጥ ቃል የገባውን በእርግጥ ሊቀበሉ ይችላሉ”

ከሕግ በታች ያሉ

ይህ የሙሴን ሕግ የመታዘዝ ግዴታ ያለባቸውን የአይሁድን ሕዝብ ይመለከታል፡፡

እነዚያ የአብርሃምን እምነት የሚጋሩ ናቸው

ይህም አብርሃም ከመገረዙ በፊት እንዳደረገው ሁሉ እምነት ያላቸውን ያመለክታል። “አብርሃም እንዳደረገው ያመኑ”

የእኛ ሁሉ አባት

እዚህ ላይ “የእኛ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጳውሎስንና አይሁድን በሙሉ እንዲሁም በክርስቶስ ያመኑ አይሁድ ያልሆኑትን ሁሉ ነው፡፡ አብርሃም የአይሁድ ሕዝብ በሥጋ አባታቸው ነው፣ ነገር ግን እርሱ ለሚያምኑ ሁሉ መንፈሳዊ አባት ነው፡፡

እንደ ተጻፈው

በተጻፈበት ቦታ ግልጽ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲሁም ይህን በአድራጊ ቅርፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። “አንድ ሰው በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ጻፈው”

እኔ አንተን ሠራሁህ

እዚህ ላይ “አንተን” የሚለው ቃል ነጠላ ሲሆን የሚያመለክተው አብርሃምን ነው፡፡