am_tn/rom/04/13.md

1.4 KiB

ወራሾች

እግዚአብሔር ቃል የገባላቸው ሕዝቦች ልክ ከቤተሰብ አባል ንብረትንና ሀብትን እንደሚወርሱ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

ነገር ግን በእምነት በሚሆነው ጽድቅ በኩል

“ቃል ኪዳኑ መጣ” የሚሉትን ቃላት በመጀመሪያው ሐረግ እንረዳዋለን፡፡ በተዘዋዋሪ መንገድ የተጠቀሱትን ቃላት በመጨመር ይህንን ልትተረጉመው ትችላለህ፡፡ “ነገር ግን ቃል ኪዳኑ የመጣው እግዚአብሔር እንደ ጽድቅ አድርጎ በሚቆጥረው እምነት በኩል ነው”

እነዚያ በሕግ የሚኖሩ ወራሾች ከሆኑ

እዚህ ላይ “በሕጉ የሚኖሩ” የሚያመለክተው ሕግን መታዘዝ ነው፡፡ “ሕጉን የሚታዘዙ እነርሱ ምድርን የሚወርሱት ከሆኑ”

እምነት የማይጠቅም፣ እናም ተስፋው ከንቱ ነው

“እምነት ዋጋ የለውም፣ ተስፋውም ትርጉም የለሽ ነው”

ምንም መተላለፍ የለም

“መተላለፍ” የሚለውን ረቂቅ ስም ለማስወገድ እንደገና ሊጠቀስ ይችላል። “ማንም ሕጉን ሊጥስ የሚችል የለም” ወይም “ሕጉን አለመታዘዝ ፈጽሞ አይቻልም”