am_tn/rom/04/11.md

1.4 KiB

ሳይገረዝ በነበረው ጊዜ ቀድሞ ያገኘውን እምነት የጽድቅ ማኅተም የሚያሳይ ነው

እዚህ ላይ “የእምነት ጽድቅ” ማለት እግዚአብሔር እንደ ጻድቅ አድርጎ ይመለከተው ነበር፡፡ “ከመገረዙ በፊት በእግዚአብሔር በማመኑ ምክንያት እግዚአብሔር እንደ ጻድቅ አድርጎ የሚቆጥርበት ምልክት ነው”

ምንም እንኳ ያልተገረዙ ቢሆኑም

ምንም እንኳ ባይገረዙም

ይህ ማለት ጽድቅ ለእነርሱ ይቆጠራል ማለት ነው

ይህ በአድራጊ ቅርፅ ሊተረጎም ይችላል። “ይህ ማለት እግዚአብሔር እንደ ጻድቃን ይቆጥራቸዋል ማለት ነው”

አብርሃም የተገረዙት አባት ሆነ

እዚህ ላይ “መገረዝ” የሚያመለክተው በአይሁድም ሆነ በአሕዛብ በእግዚአብሔር እውነተኛ አማኞች የሆኑትን ነው፡፡

የአባታችንን የአብርሃምን የእምነት ምሳሌ ተከተሉ

እዚህ ላይ “የእምነት እርምጃ ተከተሉ” ማለት የአንድን ሰው ምሳሌነት መከተል ማለት ነው። “የአባታችንን የአብርሃምን የእምነት ምሳሌ የሚከተሉ” ወይም “አባታችን አብርሃም እንዳደረገው እምነት ያላቸው”