am_tn/rom/03/31.md

995 B

አያያዥ መግለጫ

ጳውሎስ ሕጉን በእምነት ያጸናል፡፡

እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን?

ጳውሎስ ከአንባቢዎቹ አንዱ ሊኖረው የሚችለውን ጥያቄ ይጠይቃል። “አንድ ሰው እምነት ስላለን ሕጉን ችላ ማለት እንችላለን ይል ይሆናል።”

ፈጽሞ አይሆንም

ይህ አገላለጽ ቀደም ሲል ለተነሣው የአጻጻፍ ጥያቄ እጅግ ጠንካራ ምላሽ የሚሰጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ ልትጠቀምበት የምትችል ተመሳሳይ አገላለጽ በቋንቋህ ሊኖርህ ይችላል፡፡ “ይህ በእርግጥ እውነት አይደለም” ወይም “ፈጽሞ አይደለም”

ሕጉን እንደግፋለን

“ሕጉን እንታዘዛለን”

እኛ

ይህ ተውላጠ ስም ጳውሎስን፣ ሌሎች አማኞችን እና አንባቢዎችን ይመለከታል።