am_tn/rom/03/29.md

1.2 KiB

ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ አምላክ ብቻ ነውን?

ጳውሎስ እነዚህን ጥያቄዎች ለአጽንኦት ለመስጠት ይጠይቃል፡፡ “እናንተ አይሁዳውያን፣ በእርግጥ እግዚአብሔር የሚቀበለው እናንተን ብቻ እንደሆነ ማሰብ የለባችሁም!”

የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፣ የአሕዛብም ደግሞ ነው

ጳውሎስ ነጥቡን ለማጉላት ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ “እርሱ ደግሞ አይሁድ ያልሆኑትን፣ አሕዛብንም ይቀበላል”

እርሱ መገረዝን በእምነት ያጸድቃል፣ አለመገረዝንም ደግሞ በእምነት

እዚህ ላይ “መገረዝ” አይሁድን የሚያመለክት ምሳሌአዊ አነጋገር ሲሆን “አለመገረዝ” ደግሞ አይሁድ ያልሆኑትን የሚያመለክት ምሳሌአዊ አነጋገር ነው፡፡ “እግዚአብሔር አይሁዶችንም ሆኑ አይሁድ ያልሆኑትን በክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት በኩል በፊቱ ያጸድቃቸዋል”