am_tn/rom/03/27.md

1.2 KiB

ትምክህት እንግዲህ ወዴት አለ? ፈጽሞ የለም

ጳውሎስ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው ሰዎች ሕጉን በመታዘዝ የሚኩራሩበት ምንም ምክንያት እንደሌለ ለማሳየት ነው፡፡ “እንግዲያው እነዚያን ሕጎች ስለታዘዝን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ እንዳገኘን የምንኮራበት ምንም መንገድ የለም፡፡ ትምክህት ተወግዶአል”

በምን መሠረት? በሥራ ነውን? አይደለም፣ ነገር ግን በእምነት መሠረት እንጂ

ጳውሎስ የሚያነሣቸው እያንዳንዱ ነጥብ በእርግጠኝነት እውነት መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት እነዚህን መልስ የማይሰጥባቸውን ጥያቄዎች ይጠይቃል ይመልሳልም፡፡ ይህንን ጳውሎስ ሊላቸው የፈለጋቸውን ቃላት አድራጊ ቅርፅን በመጠቀም ልትተረጉማቸው ትችላለህ። “ትምክህትን የምናስወግደው በምን መሠረት ነው? በመልካም ሥራችን ምክንያት ልናስወግደው ይገባልን? ፈጽሞ፣ ይልቁንም በእምነት ልናስወግደው ይገባናል”