am_tn/rom/03/23.md

1.2 KiB

ከእግዚአብሔር ክብር ጎድለዋል

እዚህ ላይ “የእግዚአብሔር ክብር” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር ሲሆን፣ የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን አምሳያ እና ባሕርይውን ነው። “እግዚአብሔርን ከመምሰል ጎደሉ”

በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል በጸጋው እንዲያው ይጸድቃሉ

እዚህ ላይ “መጽደቅ” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ መሆንን ነው፡፡ ይህንን በአድራጊ ቅርፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። “እግዚአብሔር በእርሱ ፊት ትክክለኛ ይሆኑ ዘንድ እንደ ነጻ ስጦታ ሰጥቷቸዋል፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነጻ አውጥቶአቸዋልና።”

እነርሱ በነጻ ጸድቀዋል

ይህ ማለት እነርሱ የጸደቁት የራሳቸው ሊያደርጉት ወይም የተገባቸው ሳይሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔር በነጻ ያጸድቃቸዋል፡፡ “በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆኑት ሊያገኙት የሚገባቸው ሆኖ አይደለም”