am_tn/rom/03/21.md

1.8 KiB

አያያዥ መግለጫ

እዚህ ላይ “ግን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጳውሎስ መግቢያውን መጨረሱንና ዋንኛውን ነጥብ መጀመሩን ነው፡፡

አሁን

“አሁን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሱስ ወደ ምድር ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡

ያለ ሕግ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጦአል

ይህንን በአድራጊ ቅርፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። “ሕጉን ሳትታዘዝ እግዚአብሔር በእርሱ ፊት ትክክል የምትሆንበትን መንገድ አሳውቆአል”

በሕጉ እና በነቢያት ተመስክሮለታል

“ሕጉና ነቢያት” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት በሙሴና በነቢያቱ በአይሁድ ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተጻፉትን ከፊል የእግዚአብሔር ቃል ነው። ጳውሎስ እዚህ ላይ የሚገልጻቸው በፍርድ ቤት ቆመው እንደሚመሰክሩ ሰዎች አድርጎ ነው፡፡ ይህንን በአድራጊ ቅርፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። “ሙሴና ነቢያት የጻፉት ይህንን ያረጋግጣሉ”

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በኩል የሆነው የእግዚአብሔር ጽድቅ

እዚህ ላይ “ጽድቅ” ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ትክክል መሆን ማለት ነው፡፡ “በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በእግዚአብሔር ፊት ትክክል መሆን”

ልዩነት የለምና

ጳውሎስ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ሁሉንም ሰዎች በተመሳሳይ መንገድ እንደሚቀበል ነው፡፡ “በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ፈጽሞ ልዩነት የለም”