am_tn/rom/03/15.md

1.5 KiB

የእነርሱ . . . የእነርሱ . . . እነዚህ ሰዎች . . . የእነርሱ

እነዚህ ቃላቶች የሚያመለክቱት በሮሜ 3፡9 ውስጥ ያሉትን አይሁዶች እና ግሪኮችን ነው፡፡

እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው

እዚህ ላይ “እግሮች” የሚለው ሰዎቹን እራሳቸውን የሚያመለክት አባባል ነው፡፡ “ደም” የሚለው ቃል ሰዎችን መግደል የሚያመለክት ምሳሌ ነው፡፡ “ሰዎችን ለመጉዳት እና ለመግደል የፈጠኑ ናቸው”

ጥፋትና መከራ በመንገዳቸው ላይ ናቸው

እዚህ ላይ “ጥፋት እና መከራ” የሚሉት ቃላት የሚወክሉት ሰዎቹ በሌሎች ሰዎች ላይ የሚያስከትሉትን ጉዳትና መከራ ነው፡፡ “ሌሎችን ለማጥፋት እና መከራ ሊያደርሱባቸው ይጥራሉ”

የሰላም መንገድ

“ከሌሎች ጋር በሰላም እንዴት መኖር እንደሚቻል።” “መንገድ” ጎዳና ወይም መተላለፊያ ነው፡፡

በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም

እዚህ ላይ “ፍርሃት” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ማክበር እና እርሱንም ለማክበር ፈቃደኝነትን የሚወክል ነው፡፡ “ሁሉም ሰው ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም”