am_tn/rom/03/11.md

1.1 KiB

የሚያስተውል አንድስ እንኳ የለም

ትክክል የሆነውን ነገር የሚያስተውል የለም። “ትክክለኛ የሆነውን ነገር የሚያስተውል ማንም የለም”

እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም

እዚህ ላይ “እግዚአብሔርን መፈለግ” የሚለው ሐረግ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት መፍጠርን የሚያመለክት ነው፡፡ “ማንም ከእግዚአብሔር ጋር እውነተኛ ኅብረት የውለም”

ሁሉም ትችሳስተዋል

ይህ ሰዎቹ እግዚአብሔርን ማሰብ እንኳን እንደማይፈልጉ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ እርሱን ለማስወገድ ይፈልጋሉ። “ሁሉም ከእግዚአብሔር ርቀዋል”

እነርሱ በአንድነት የማይጠቅሙ ሆነዋል

ማንም መልካም የሆነውን ስለማያደርግ ለእግዚአብሔር የማይጠቅሙ ናቸው። “እያንዳንዱ ለእግዚአብሔር የማይጠቅም ሆኗል”