am_tn/rom/03/09.md

1.0 KiB

አያያዥ መግለጫ

ጳውሎስ በአጠቃላይ ሲናገር፣ ሁሉም ኃጢአተኛ ነው፣ ማንም ጻድቅ የለም፣ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም ይላል፡፡

እንግዲውስ? ለእራሳችንን ይቅር ማለት እንችላለን?

ጳውሎስ አሳቡን ለማጉላት እነዚህን ጥያቄዎች ይጠይቃል፡፡ “እኛ አይሁዳውያን አይሁዳውያን በመሆናችን ብቻ ከእግዚአብሔር ፍርድ እናመልጣለን ብለን ለማሰብ መሞከር የለብንም!”

ፈጽሞ

እነዚህ ቃላት በቀላሉ “አይደለም” ከምንለው ጠንካራ ናቸው፣ ነገር ግን እንደ “በፍጹም አይደለም!” እንደሚለው ጠንካራ አይደለም።

ይህ እንደ ተጻፈው ነው

ይህንን በአድራጊ ቅርፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። “ይህ ነቢያት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ጻፉት ነው”